Wednesday, September 30, 2009

እውነቱ ሲነገረው የማይወድ የሀሰት ልጅ ነው

እውነቱ ሲነገራችሁ እውነቱን የነገራችሁን ቶሎ ብላችሁ አንባቢን ለማወናበድ እንደለመዳችሁት የማታውቁትን ሰው ደስ ያላችሁን ስም ይልቁንም ለናንተ የሚስማማውን ስም ትቀባላችሁ።

እኔ ንጹህ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጅ ነኝ። ተሀድሶም አላልኩም ወይም መናፍቅ ሆኜ አላውቅም። በሐይማኖቴ ጸንቼ ያለሁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ከአባቶች እግር ስር ቁጭ ብዬ የምማር፤ ሳይገባኝ ግን በቸርነቱ ብዛት በቤቱ የማድግና እንደ አቅሜ የማገለግል ብላቴና ነኝ።

ይልቁን የሚታደሰው በአመጻ የደነደነ ተሳዳቢ፣ ሸረኛ፣ የማያምን ግን በአማኞች መካከል አማኝ መስሎ አመጻን የሚያስነሳ ልብ ነው። ለምሳሌ የዘመኑ ፈሪሳዊያኖች ማህበረ ሰይጣኖች፤ በአማኞችና በቤተ ክርስቲያን ስም የሚነግዱ ናቸው።

«የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።» ሮሜ 12፥2

በጎና ደስ የሚያሰኘውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ በአመጻ፣ በስድብ፣ ጳጳሳትንና አበው ካህናትን በመሳደብ ልታውቁ የምትደክሙ የጥፋት መልእክተኞችን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህንን ዓለም አትምሰሉ አለ። ከአመጻ እራስን ዝቅ ወደማድረግ፣ ጳጳሳትንና አበው ካህናትን ከመሳደብ ማክበርና ብሎም እግራቸው ስር ቁጭ ብሎ መማር። የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው አለ እንጂ ስደቧቸው ወይም በሀሰት ክሰሷቸው የሚል ቃል የለም። ካለ እስኪ እዚህ ጋር ይገኛል በሉን፣ መጽሐፍ ቅዱስ ፈቅዶልን ነው በሉን።

የምትሳደቡት ግን ከልባችሁ ሞልቶ የተረፈ የአመጻ ፍሬያችሁ ስለሆነ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ተመዝግቦ እንደምናገኘው ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ይላል፥

«ዛፍ ከፍሬዋ ትታወቃለችና ዛፍዋን መልካም፥ ፍሬዋንም መልካም አድርጉ፥ ወይም ዛፍዋን ክፉ ፍሬዋንም ክፉ አድርጉ። እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ክፉዎች ስትሆኑ መልካም ለመናገር እንዴት ትችላላችሁ? በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራልና። መልካም ሰው ከልቡ መልካም መዝገብ መልካም ነገርን ያወጣል፥ ክፉ ሰውም ከክፉ መዝገብ ክፉ ነገርን ያወጣል። እኔ እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል፤ ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና ከቃልህም የተነሣ ትኰነናለህ።» የማቴዎስ ወንጌል 12፥33-38

ለዚህ ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህንን ዓለም አትምሰሉ ያለው። ልባችሁ ታድሶ መልካም ፍሬን ቢያፈራ ኖሮ ቀና ብላችሁ በድፍረት የሐይማኖት አባቶችን ባልተሳደባችሁ ነበር። ያለ ስልጣናችሁም መናፍቅ የሚል ስም ባልቀባችኋቸው ነበር። እነርሱ ይህ አይደንቃቸውም ሊቀ ካህናቱም(ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም) ይህንኑ ተብሎ ተሰድቧልና ለነሱ ስለ እውነት መሰደብ ክብር ነው። «ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ። ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።» የማቴዎስ ወንጌል 5፥11፡12 ከዝንብ ማር አንጠብቅም እንዲሉ አበው፤ ልባችሁ ያላፈራውን እንዴት ከአንደበታችሁ ይጠበቃል።

አሁንም እላለሁ!!! በፍርድ ቀን ነጭ ልብስ ለብሳችሁ የነፍሳችሁን ቤዛ በደስታና በዝማሬ ለመቀበል የምትሹ ሁሉ የንስሃ ጊዜ ዛሬ አይደለም ግን አሁን አዎን አሁን ነው። ነገ የኛ ለመሆኗ ምንም ዋስትና የለምንም። ክርክሩን ትተን በንስሃ ወደ ጌታችንና መድኃኒታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንቅረብ። ድህነት የሚገኘው በአድመኝነት፣ በአመጻ፣ በስድብ፣ በተንኮል፣ ንዑሰ ክርስቲያኖችን በማታለል፣ በአጠቃላይ በክፉ ፍሬ አይደለም። በንስሀ ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ ብቻ ነው።

ቅዱስ ዳዊት እንዲህ ይላል፥

ቅረቡ ኀቤሁ ወያበርህ ለክሙ።
ወኢይትኀፈር ገጽክሙ።
ዝንቱ ነዳይ ጸርኀ ወእግዚአብሔር ሰምዖ።

ትርጉም፥
ወደ እርሱ ቅረቡ ያበራላችሁማል
ፊታችሁም አያፍርም።
ይህ ችግረኛ ጮኸ እግዚአብሔርም ሰማው።
መዝሙር 33፥5

27 comments:

  1. Good job Ewnetu berta!!!

    ReplyDelete
  2. ምን ይሁን ምን እውነት ሲነገረው ወደኃላ የሚሸሽ ከሰይጣን ነው መጽሐፍም የሚለው ይህንኑ ነው የሚያጸናልን ለሰነፍ አትገስጽ ነው የሚለው ለምን ህፍረት ስለማያውቅ ተመልሶ ያዋርድሃልና እንዲል ጠቢብ በምሳሌ በመጽሐፉ። ጌታችን መድሃኒታችንም እንዲህ አለ እውነትን ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣቸኅል" ነው ያለ ባርነት ይሻለኛል ማለትም ምርጫው የተጠበቀ ነውንና በሰነፎች ቃላት ሳትሸነገል አንተ ግን በርታ እግዚአብሔር ካንተ ጋር ይሁን።

    ReplyDelete
  3. Actually it is not logical to spend time for such a rubish menafik. But let me do for a time.
    I saw your site Mulugeta. You know , what I percieve from your picture is you have no any spritual looking. The holly sprit is completely departed from you. It seems you are under devil.
    I read no good from you. You are good nor nothing. You did nothing for your church. you don't have any history even when you were in EOTC. why you defeated by your need. Why don't you try to govern yourself to lead your life in holly spirit. Why don't you follow Jesus christ. why don't you resemble Him. If you believe in Him why don't you do what He tought and showed to do? why you fight with EOTC/MK. Do you think
    our church will be abolished by such fool guys? or do you think these Menafik, tehadeso and muslim will defeat the Church. Don't you read " yegehanem dejoch ayichiluatim"?. Can you tell me anything wrong that MK did and our church face a problem due to MK? Who preveal those wicked works of our opponents/devils ,is it you or MK?
    Can you tell us any good job you did for our church?. Do you thing whites believe in Jesus Christ as creature of the world? Do you think civilization of westerlis due to they are protestans so that they worship God correctly?
    So mulugeta please get out of darkness you will bring nothing difficult to our church. It is kept by Lord. It is 2000 yours since we believe in God. this is 1500 years before your leader luther comes to this world for betray.

    come to your mind. God will forgive you. Don't kill your mother as "Efugnit" follow either your Lord or money you cannot follow both.

    In addition you are advertising your evil books with this blog. "hodam"
    Yetifat lij wolde Areos. Kehadi yihuda. lenegeru enkuan ante yihudam ke geta egir sir tekemito temiro kidotal. Tera sewu neh?. Do you see, you several times witness as if you are not mulugeta in your wicked name ewunetu. foolish it is clear for everybody. But you are foolish you didn't understand as if others understand.

    So come to you. come to your heart.
    May God forgive you.

    ReplyDelete
  4. Dear Ewunetu, it is good to write but you are in the wrong path. You can not make Jesus happy with out having loving your brothers. No where in the bible says insult people. But you are insulting people any time. May God Open your heart for love.

    ReplyDelete
  5. hello dear bloggers! please try to compare the writting style of ewunetu and gebru(third from the top)i definately think that is one person in two different name.

    ReplyDelete
  6. To the Anonymous who wrote next to gebru: you are very nonsense. You don't even read. You just type your full of hatred. Whoever is the blogger told you that he/she is not Deacon Mulugeta, he/she even said that he/she doesn't know Deacon Mulugeta. If you want to defend MK, why don't you talk about MK. And another thing you try to make one EOTC and MK. Hey they are very very very very different. EOTC is a church. MK is just a mahiber that was established by military; and now disliked by His Holiness Abune Paulos; whether you like him or not he is no Patriarch of EOTC. The blogger also told us to read "Mahibere Kidusan or Mahibere Seytan". Please stop connecting EOTC and MK. You sometimes when I think about writings like yours, I start wondering about MK. I need to read the book mentioned and find out the truth.

    Anyways, hear are my suggestion to you and your friends:
    1. READ before you type.
    2. Know the material or issues before you talk about it, unless you sound very stupid.
    3. Define yourself as EOTC believer or MK believer.
    4. Stop cursing like stupid people.
    5. Have some hummer for the words you are using.
    6. You said trash for others writing but yours is the one is trash. So write something that makes sense.
    7. The last but not the least; improve you language or use Amharic. If you don't know English you don't have type English that doesn't make you look intelligent or educated.

    ReplyDelete
  7. ለታዛቢው
    መታዘብ ጥሩ ነው ከመታዘብ ብዙ ማየት ይቻላል። በትክክለኛ መንገድ ላለመሄዴ አንተ የተሰማህን አልህ፤ እኔ ደግሞ ያመንኩበትን እላለሁ። እኔ ማንንም በሰውነቱ አልጠላም ይህንን ደግሞ ደጋግሜ ብያለሁ። ደግሞም እኔ ሰዎችን insult አላደረግሁም። ማህበሩን ግን አዎን፤ ስራውን ስለማውቅ አምንበታለሁ። እግዚአብሔር ልቤን እንዲከፍትልኝ ላልከው ስለመልካም ምኞትህም አመሰግንሃለሁ። አሜን ብያለሁ።

    ከታዛቢው ቀጥሎ ለጻፈው Anonymous
    በአማርኛ ስለጻፍን ወይስ የመጸሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ስለጠቀስን አንድ ሰው በሁለት ስም ተጠቅሞ ያልከው። ወይንስ ደግሞ እውነትን ስለተናገርን ይሆን። ለማንኛውም እውነቱን ለመረዳት ብትሻ ይገልጥልሃል። በጸሎት ለምን ይሰጥሃል። አባቶችንም ጠይቅ፤ መጠየቅ ማንን ጎዳ?

    ReplyDelete
  8. I used to hear that Satan exists in the form of evil spirit and took the flash of Snake when he led our Mother Eve to the wrong. Now, I observed that Satan is working hard in this blog. Ene min elalehu, yebetekirstian Amilak, kihudetachihun aswegido wed ewinetu yamitachihu. Yebetekrstianim telat kemehon yadinachihu.

    ReplyDelete
  9. yes, I am sure you did hear; not only hear you are in it. As long as you are part of Mahibere Sytan then you are in it. It is not as you said that this blog is. This is revealing the truth. I am sure the blogger will work more on it.

    What do you see wrong on this blog? Have you read carefully before you talk? I don't think so. Please take your time and read the article first before you talk like stupid. READDDDDDDDD

    STOP fulling yourself!!! OPEN your eyes. READ, SEE, ANALYZE, then give your comment.

    THINK, THINK, THINK, don't just talk this is not mahibere seytan gubae.

    ReplyDelete
  10. Le"kesashu"
    I will try to improve my english language. Ofcourse I am not that much bothering about it because this is my second language. And being fluent speaker of English doesn't imply ones capacity. Though, I shall try. But I proud of my language. Anyways your language is also not much better than mine. but you are addicted to haterade and insulting others. that is why you try to say me to improve my language. Bye the way language is nothing but a means of communication. For that matter you well understood my ideas. that is what I want.
    I will write you in Amharic when I have the software. I am not feeling shame usning Amharic but proud of it.

    Bye the way if you are really Tewahedo but anti MK , I am fully interested to discuss everything constructively and properly with you.

    Stay blessed.

    ReplyDelete
  11. Le"tekesashu"
    Stile you didn't improve you language. You are right language means of communication; but if you don't type right how are we going to communicate. It takes our time to read your broken language. "kefitifitu fitu yilu yelem" anyways let's go back to the topic given by the blogger.

    ReplyDelete
  12. ይህንን አጭር የማህበረ ቅዱሳን ድራማ በደጀ ሰላም ላይ ለጥፌላቸው ነበረ ግን ዲሊት አደረጉት እናንተ ግን እንደማታደርጉብኝ ተስፋ አደርጋለሁ። ታሪኩ ለቀልድ የተጻፈ ሳይሆን የእውነት ታሪክ ነው፤
    ማህበረ ቅዱሳኖች ወይም የዚህ ብሎጎች እንዳሉት ማህበረ ሰይጣኖች ሳይማሩ አስተማሪዎች የሆኑት በልባቸው ድንዳኔ ነው። አንድ የማህበረ ቅዱሳን አመራርና መምህራቸው ያደረገውን ልንገራችሁ። መቼም ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው አይደል የሚባለው። ማን እንደሾመው በውል ባላውቅም ሲጠሩት መምህር ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ትሉታል። ታዲያ በአንድ ወቅት እንደ መምህራኖቹ ሊቅ መስሎ ለመታየት በጨርቅ መስሎት አለባበሱን አሳምሮ በአንድ ከባህር ማዶ ወደሚገኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቤተ መቅደስ ዘው ብሎ ጥልቅ ይላል። በዚያ የነበሩ አንድ አባት ስላላወቁት ማን ትባላለህ ብለው ይጠይቁታል እርሱም መምህር ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እባላለሁ ብሎ ይመልሳል። ታዲያ እኒህ አባት እንግዳ ዲያቆን መጣ ብለው እንኳን ደህና መጣህ፤ በል ከኛ ጋር ትቀድሳለህ እግዚአብሔርን አመስግን ቢሉት እርሱም አይ እኔ አልቀድስም አይሆንልኝም ብሎ እርፍ። እሳቸውም ምን ነው የኔ ልጅ ቢሉት፤ ቅዳሴ አልችልም ማስተማር ብቻ ነው የምችለው ብሎ እርፍ። እንደነገሩ ሁሉም አልፎ ስርዓተ ቅዳሴ ተጠናቅቆ ውጭ ከወጣ በኋላ እራሱን ሲያጋልጥ እኒህ አባት ተሐድሶ ናቸው፣ መናፍቅ ናቸው ብሎ ማስወራት ጀመረ። እንዲህ ነው እንግዲህ የተርታ ስም ሲያወጡ። ሲያጋልጧቸው ውጭ ወጥተው እያጋለጥን ነው ብለው ያወራሉ። ታዲያ ዳንኤል ክብረት ማን ነው? በእውነት ይንን ዲያቆን ትሉታላችሁ? መምህርነቱስ ከየት የመጣ ይሆን? ያላዋቂ ሳሚ ...

    እባካችሁ እናንተም ዲሊት እንዳታደርጉት ሌሎችም ይወቁት።

    ReplyDelete
  13. YOU ARE REALLY HERETIC!mulugeta.

    ReplyDelete
  14. እውነት መናገሬ ነው እንደ ኃጢአት የታየብኝ። የእውነት አምላክ ያያል፤

    ነቢያትን የሚያቃልል ቢኖር ከዋሕድ (ከወልድ) መዓት እራሱን ያርቅ፤ ነፍሱንም ያድን። መስቀልን አይበድል፤ ከእግዚአብሔር መዓት ይራቅ፤ የሚያየን ብርሃን አብ ከልጁ ጋር ቤተ ክርስቲያንን ከሚጎበኙ ከቅዱሳን መላእክትም ጋር አለና። ነፍሳችሁን ተመልከቱ ሰውነታችሁንም ንጹሕ አድርጉ፤ የባልንጀራችሁንም በደል አታስቡ፤ ማንም ከወንድሙ ጋር በቁጣ እንዳይኖር አስተውሉ፤ እግዚአብሔር ያያል፤ ልቦናችሁን ከፍ ከፍ አድርጉ፤ ...

    ReplyDelete
  15. Dear: Ewnetu please don't be discarage by Ferisawian. Forget about you, Fersawiyan even they were insulting his disayples and our Lord juses christ. What is new? But,

    " Eskemecheresha yemisena eresu yedenale"

    Ayzoh yewent Amlak nesa yawtahal
    Degmos manen newu yemiteferaw? segana demen? atefera. Manam selene kefuwn hulu bewushet binagerubachehu bsuan nachehu.

    Befetena Sena
    Legizaw newu enji hulum yalfalena.

    ReplyDelete
  16. «የሌባ ዓይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ» ማህበረ ሰይጣኖች ጥፋታቸውን ከማመንና ንስሃ ከመግባት ይልቅ እራሳቸውን በማታለል በስድብና በአመጻ ሕይዎት ለመኖር የቆረጡ ይመስላሉ። ምን ተብሎ እስኪነገራቸው ድረስ እንደሚጠብቁ አይገባኝም። ለነገሩ በጥቅምና በከንቱ ውዳሴ የተሳሰሩ ስለሆኑ እውነቱን መቀበል ያስቸግራቸዋል። ለማንኛውም ቃሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ነውና እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ቢኖሩ ይነኩበታል ወደ እውነትም ይመጣሉ፤ ስለዚህ በርታ ...

    ReplyDelete
  17. Ewnetu I appriciate your courage and firm foundation. You are the great witness for our Mother Church. Be positive, be focused and above all be humble before God. As our Fathers shown us, you have to be humble before God. MK is from Devil. They are using Demonic power for their goal. But as you know our Lord Jesus Christ crushed the power of Demons. He will crush the power of Debtera's evil spirit.

    ReplyDelete
  18. For the above anonymous, Thank you for your comment, and I will do my best to be positive, focused and humble before God. Please remember me in your prayer. May the Almighty God gives us strength, love, peace, and unity.

    ReplyDelete
  19. Ewunetu and his followers,

    I am just looking at your comments, I saw the book written by Deacon Mulugeta that it is rubbish. Don't take me as member of MK, I am just a christian who want to be with the truth. And you guys instead of blaming MK, why not you work together for the better achievement in the church. Though I am not Tehadiso who exaggerate problems in the church, I share few problems in the church that should be improved. However defaming or blaming each other will not bring any solution as you guys are doing.

    God is always God. He sees every one in one eye. He has the same Justice for every one in the world. The best thing we should hold is love to our brothers. One cannot make God Happy with out Love to brothers.!!!

    Let us work together and make mutual understanding among us.

    ReplyDelete
  20. ሰላም ላንተ ይሁን ታዛቢው

    በዲያቆን ሙሉጌታ የተጻፈውን «ማህበረ ቅዱሳን ወይስ ማህበረ ሰይጣን» የሚለውን መጽሐፍ ለምንድን ነው "rubbish" ያልከው? እውነትን ስለተናገረ ነው? እስኪ አንብበኸው ከሆነ የትኛውን እውነት ነው መቀበል ያቃተህ? ወይም ማንበብህን የሚጠቁም የተወሰኑ ሃሳቦችን ጥቀስና በዚህ ምክንያት አልቀበላቸውም በለን።

    ለምንድን ከነሱ ጋር ስሩ እንዳልክ አልገባኝም። እኛ እኮ «ግብራቸው ከዲያብሎስ ነው» ነው የምንለው።

    ከነሱ ጋር አባቶችን ተሳደቡ ነው የምትለው?
    ወይስ ከነሱ ጋር ቤተ ክርስቲያንን ዝረፉ ነው የምትለው?
    ወይስ ከነሱ ጋር የፈሪሳዊያንን ትምህርት አስተምሩ ነው የምትለው?
    ወይስ ከነሱ ጋር እህቶችን በክርስትና ስም እየቀረባችሁ ክብራቸውን አዋርዱ ነው የምትለው?
    ወይስ ከነሱ ጋር አባቶችንና ምእመናንን በዘርና በውሸት ወሬ አጣሉ ነው የምትለው?
    ወይስ ከነሱ ጋር ጳጳሳትን፣ ካህናትን፣ መምህራንን እና ሌሎችንም ምእመናንን እውነትን ስለተናገሩ ብቻ ተሐድሶና መናፍቅ እያላችሁ ባልሆኑት ስም ቀቡዋቸው ነው የምትለው?

    ኧረ ስንቱ? ...

    ጥያቄህ አልገባኝም።

    እኛ ግን ከብፁዓን አባቶቻችን፣ ከካህናቶቻችን፣ ከመምህሮቻችን ጋር ለተሻለ ነገር እንሰራለን። ያም የሚሆነው በአንዲት ቤተ ክርስቲያን ጥላ ስር ሆነን ነው እንጂ በሃይማኖት አይሉት በፖለቲካ ማህበር ስር ሆነን አይደለም። አይስማማንም። አይዋጥልንም።

    ከሁሉም በላይ ደግሞ ለሰላም፣ ለፍቅር፣ ለአንድነት እንጸልያለን።

    «...እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ቀድሞ የተነገረውን ቃል አስቡ፤ እነርሱ። በመጨረሻው ዘመን በኃጢአተኝነት እንደ ገዛ ምኞታቸው እየሄዱ ዘባቾች ይሆናሉ ብለዋችኋልና። እነዚህ የሚያለያዩ ሥጋውያንም የሆኑ መንፈስም የሌላቸው ሰዎች ናቸው። እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ። አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፥ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ፥ አንዳንዶችንም በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ማሩ። ...»
    የያዕቆብ ወንድም የይሁዳ መልእክት ፩፥፲፯-፳፬

    ሙሉውን ብታነበው ደግሞ ምን እያልንና ለምን እንደምንቃወማቸው ትረዳዋለህ።

    ReplyDelete
  21. ውድ እውነቱ ካለ መጥሐፉን አንብቤዋለሁ።ሳላነብ የምናገር ሰው አይደለሁም። ስለምክርህም አመሰግናለሁ። ነገር ግን መፅሐፉን ሳነበው ምንም ታማኒነት አያቀርብም ለምሳሌ አባቶችን አሳደደ ይላል እንጂ እነ ማንን አሳደደ የሚለውን አይገልጽም። ከዚህም በተጨማሪ ተራ የሆኑ ስድቦች ይዞ ይገኛል። ለኔ ይህ ጥቅም አልባ ነው። ለማኛውም እኔ የእነሱ ጠበቃ አይደለሁም። ግን ለአንዲት ቤተ ክርስቲያን እንሰራለን የሚሉ ሁሉ በመነጋገር ችግሮቻቸውን ይፈታሉ የሚል ሐሳብ አለኝ። የሀይማኖት ልዩነት እስከሌለ ድረስ። ለነገሩማ የሃይማኖት ልዩነት እንከን ቢኖር መጽሐፍ ቅዱስ እስከተከተልን ድረስ አንድ መሆን ይቻል ነበር የሚሰማ የለም እንጂ።

    ከጨረስሁ በሃላ አንድ ጥያቄ መጣልኝ ከላይ የጻፍሀቸውን እንድታብራራልኝ ነው። ምክነያቱም እያንዳንዳቸውን ለመረዳት እፈልጋለሁ።አንተው ራስህ ስትመልስልኝ ስለእነርሱ የሚከተለውን ብለሐኛል፡

    ከነሱ ጋር አባቶችን ተሳደቡ ነው የምትለው? - አባቶችን የትኞቹን ነው የሚሳደቡት እባክህ ግለጽልኝ ከመረጃ ጋር

    ወይስ ከነሱ ጋር ቤተ ክርስቲያንን ዝረፉ ነው የምትለው? - ቤተ ክርስቲያን ይዘርፋሉ የሚል እምነት በፍጹም የለኝም ምክነያቱም ራሳቸው ገንዘባቸውን ሳይቀር ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚያውሉ እየተባለ ነው አዲስ አበባ የሚወራው እና ቤተ ክርስቲያን ይዘርፋሉ ነው የምትለኝ?

    ወይስ ከነሱ ጋር የፈሪሳዊያንን ትምህርት አስተምሩ ነው የምትለው? የፈሪሳውያን ትምህርት ወንጌል የሌለበት የማያድን ክርስቶስን ያላወቀ ለህግ እና ለስርዓት ብቻ የቆመ እንደሆነ አውቃለሁ። እና ማቆች ፈሪሳውያን ናቸው የወንጌል አስተምሀሮ አያውቁም? ምን አልባት ይህ ሊሆን ይችላል ምክነያቱም አንድ ወዳጀም ለስርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቀናኢ ናቸው ሲል ሰምቸዋለሁ በቅርብ የማውቀው ሰው።

    ወይስ ከነሱ ጋር እህቶችን በክርስትና ስም እየቀረባችሁ ክብራቸውን አዋርዱ ነው የምትለው? ጉድ ይንንም ያደርጋሉ? አቤት የትኞቹ አባሎቻቸው ናቸው ይህን የሚያደርጉት እኔስ ስሰማ በጣም በጾም በጸሎት የተጠመዱ ናቸው ነበር ሲባል የሰማሁት እባክህ ይህን ስም ሳትጠቅስ እንዲህ ያደረገ ካለ ጻፍልኝ።
    እኔም እንዳውቅ


    ወይስ ከነሱ ጋር አባቶችንና ምእመናንን በዘርና በውሸት ወሬ አጣሉ ነው የምትለው?

    ወይስ ከነሱ ጋር ጳጳሳትን፣ ካህናትን፣ መምህራንን እና ሌሎችንም ምእመናንን እውነትን ስለተናገሩ ብቻ ተሐድሶና መናፍቅ እያላችሁ ባልሆኑት ስም ቀቡዋቸው ነው የምትለው?

    እነርሱ ያለሆነውን መናፍቅ ታድሶ ይላሉ እንዴ ይህ ሊሆን ይችላል ምክነያቱም የእነ አባ ዮናስን ፊልም እነሱ እንዳወጡ አይቻለሁ እና ምን አልባት ሌላውንም ሳይለዩ ስም ሊሰጡ ይችላሉ። ለማነኛውም እስኪ እንነጋገር እና አንተ ንገረኝ እኔም ልስማህ።ግን እኔ የምሰማው እያጣራሁ ነው፤ማለቴ መረጃ የሌለው ጉዳይ አልሰማም አዕምሮየ አያምንም። የእግዚአብሔርን መኖር የክርስቶስን አለምን ማዳንና የድንግልን በድንግለና መውለድ ብቻ ነው ያለ መረጃ ያመኩት;፤

    ለክርሰቶስ ክብር ምስጋና ይሁን አንተ ወዳጀም እንድትመልስልኝ ይሁን አሜን!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  22. You MK and Mulgeta are very stipuids!!
    I know who is Mulgeta and so does MK.
    Why don't you become an attorney of the church atleast one day instead of insulting each other?

    ReplyDelete
  23. እውነቱ
    ስራህን ጌታ ይባርክ!!!
    ማህበረ ቅዱሳን ስላሞች(ኦሪታውያን) እንደሆኑ ሁሉም ሰው ያውቃል ምክንያቱም በስራ መጽደቅ ስለሚፈልጉ ልዚህ ይመስለኛል እውነት (ኢየሱስ) ተብሎ ሲነገር የሚያሳብዳቸው

    ReplyDelete
  24. አንድ ነቸው

    ማህበረ ቅዱሳን

    .በስራ መጽደቅን ያምናሉ
    .አሳማ መብላት ሃጢያት ነው ይላሉ
    .ሴት ልጅ መሸፋፈን አለባት
    .ኢየሱስ ይሚለው ስም አይስማማቸውም
    .እውነት ተናጋሪን አይወዱም
    .ሰላምን አይወዱም
    .ሲጾሙ እንድግብዞች ናቸው

    እስልምና

    .በስራ መጽደቅን ያምናሉ
    .አሳማ መብላት ሃጢያት ነው ይላሉ
    .ሴት ልጅ መሸፋፈን አለባት
    .ኢየሱስ ይሚለው ስም አይስማማቸውም
    .እውነት ተናጋሪን አይወዱም
    .ሰላምን አይወዱም
    .ሲጾሙ እንድግብዞች ናቸው

    ReplyDelete
  25. Full of scam. arrogant menafek

    ReplyDelete
  26. ያሬድ ዘክርስቶስDecember 1, 2011 at 12:41 AM

    ይሁዳም እንዳንተ ከጌታ እግር ስር ተቀምጦ ተምሮ ነበር፤፤ እንዳንተ አይነተቶች ናቸው ቤተ ክርስቲያንን የሚሸረሽሩት ጥቅምህ የተነካ መሰለኝ ለዛ ነው የጮህከው እንደዳንተ አይነቱ የውስጥ እሾክ ነው ቤ/ክንን እየበላት የያለው ፤፤ክርስቲያን ከሆንክ የግል ጥቅምህን ተውና ንስሃ ግባ ተመማኝ ለመሀሆን አትመሞክር ማህበሩ የሚታይ ስራ አለው ያንተን ምስክርነት አይሻም

    ReplyDelete
  27. Mahibere kidusan tiru bastemaru ,tihitinan bastemaru,anidinetin besebeku,sile kiristos bastemaruna sile kidisit dinigil mariyam silemesekeru,sile kidusan silemesekeru .......metifona asheberi ketebalu .....ashebarinet deg mesirat kehone tirgumu...ENEM ASHENARINETIN E-W-E-D-E-W-A-L-E-W!!!!

    ReplyDelete