Tuesday, September 29, 2009

የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ

የሚገርመው ነገር «መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ» እንዲሉ እነዚህ እራሳቸውን ማህበረ ቅዱሳን እያሉ የሚጠሩ ማህበረ ሰይጣኖች በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስር ነን እያሉ እንደ መዥገር ተለጥፈው ንጹሐን ወንድሞችንና እህቶችን በማሳሳት አባቶችን እንዲሳደቡ የሚያደርጉ አንዴ በቅዱሳን ስም እራሳቸውን ማህበረ ቅዱሳን ደግሞም የጥፋት መልእክተኞች እንደሆኑ እያወቅናቸው እራሳቸውን በሌላ ስም ደጀ ሰላም ብለው አሁንም የማጭበርበር ሥራቸውን እንደ ቀጠሉ አሉ። እኔን የሚያሳዝነኝ ግን እነሱ ለነፍሳቸው የማይራሩ መሆናቸውና እንደ ድሮው ባይሆንም አሁንም ድረስ በነዚህ ማህበረ ሰይጣኖች የሚታለሉት ወንድሞችና እህቶች ናቸው።


«አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይነቃም» እንዲሉ ለማህበሩ መሪዎች ነን ለሚሉት በመምከር ጊዜዬን አላጠፋም። በፍጹም ልባቸው እግዚአብሔርን ብለው ይቅርታ ለማግኘትና ላደረገላቸው ነገር ምስጋና ለማቅረብ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለሚመጡ በደመ ክርስቶስ የከበሩ ንጹሐን ወንድሞችና እህቶች ግን አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ጠቅሼ ለማለፍ እወዳለሁ፥


«የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው። ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው።» ወደ ዕብራውያን 1378


ቅዱስ ቃሉ «ዋኖቻችሁን» የሚለው ሰላም ለኪ ሳይሉና ሀብተ ክህነት ሳይኖራቸው በራሳቸው ፈቃድ በቅዱሳን ስም ማህበር አቋቁመው አስራት የሚሰበስቡትን ሳይሆን በነ ቅዱስ ጴጥሮስ ወንበር የተተኩትን ቅዱሳን አባቶችን እንደሆነ ይህን እውነት መገንዘብ የሚያስቸግራችሁ አይመስለኝም። እባካችሁ የነፍሳችሁ ቤዛ ወደሆነው ወደጌታችንና ወደመድኃኒታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልከቱ። እግዚአብሔር አምላክ በቅዱስ ልጁ የጠራን ለአመጻ ሳይሆን ለመዳንና ብሎም ለኛ ያዘጋጀልንን ሰማያዊ ቤት ለማውረስ ነው። ይህ ደግሞ በአመጻ፣ አበውን በመሳደብና በማዋረድ የሚገኝ አይደለም። እባካችሁ እናስተውል። ቤተ ክርስቲያን አንዲት ናት የመናፍቅና የኢአማንያን ሳይበቃ እኛ ገና ለእምነቱ ሕጻናት የሆነው ለአባቶች ህመም አንሁንባቸው። ሁሉን ትታችሁ አበውን ጠይቁ ንጹሁን እምነታችንን ያስተምሩዋችኋል። እራሳቸውን ለዚህ ቅዱስ አገልግሎት አሳልፈው የሰጡ ቅዱሳን አባቶች በክርስቶስ ፍቅርና ትህትና ያስተምሩናል። የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው። የእግዚአብሔርን ስም እየጠሩ በግብራቸው የካዱትን ሳይሆን በኑሮአቸው የሚመስሉትን ምሰሉ።

6 comments:

  1. Temesgen:

    Ewnetu you did the right thing. The commite of MS is not listing the Lord's word. Because, ones taken by seytan, they are loyal for seytan and money. So you are saving the Yewahan members from them, by teaching the word of God.

    God will save them using you. Our Lord doesn't want his children's to go in the wrong way. Even the leaders of MK, if they be came the children of God, he is merciful he will take them back.

    Ewnetu you are doing a great job. Don't discourage by some evil commentator of MK.

    God protect you from Evil
    God Protect his Holiness Aba Paulos
    God protect Aba W/Tenesaye
    God protect Aba H/Michael
    God Protect Aba Serek Berhan
    God Protect Kesis Asteraye and all of the true EOTC Fathers, Papasats, Memenans and Ethiopia.

    Deliver us From MS Amen.

    ReplyDelete
  2. ማህበረ ሰይጣኖች ወይም ደጀ በጥብጦች ካገኙ እንደሚደበድቡ ሰምተናል አይተንማል፤ ግን ደግሞ ዲያቆን ሙሉጌታ እንደሚለው ደግሞ «ለሕይወት ያለህን ጉጉት ለሞት ስታከፍለው እውነትን መናገር ትጀምራለህ» በጣም ታላቅ አባባል ነው። እውነቱን ተናግሮ ካመሹበት ማደር የሚለውን የመጀመሪያውን ርዕስ ወድጄዋለሁ። ይበል የሚያስብል ነው።

    ReplyDelete
  3. ደሮ ብታልም ጥሬዋን እንዳሉት ነው አበው ማሰቡማ የማህበሩ አባላትና የአመራር ክፍሎች ሳያስቡ ቀርተው ነው ብለህ ነው አይመስለኝም ቁምነገሩ የሚያስቡት ማንን ነው? ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እደተናገረው እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ እንዲል መልካቸው ያይደለ አመለካከታቸው አካሄዳቸውን ነበርና ሞዴላቸው የሀሰት አባት ዲያብሎስ እስከሆነ ድረስ የማህበሩ አባላትም ሆኑ አመራር ከአመጻና ከሃጢአት ባርነት ነጻ ሊሆኑ አይችሉም።

    ጅምርህ የሚበረታታ ነው ግፋበት ቁምነገር ያለው እየተገፋህ ነው ነውና በአንድ ሁለት ተብሎ የተጀመረህ እግዚአብሄር ያስደንቅሃል በርታ!

    ReplyDelete
  4. ይህንን አጭር የማህበረ ቅዱሳን ድራማ በደጀ ሰላም ላይ ለጥፌላቸው ነበረ ግን ዲሊት አደረጉት እናንተ ግን እንደማታደርጉብኝ ተስፋ አደርጋለሁ። ታሪኩ ለቀልድ የተጻፈ ሳይሆን የእውነት ታሪክ ነው፤
    ማህበረ ቅዱሳኖች ወይም የዚህ ብሎጎች እንዳሉት ማህበረ ሰይጣኖች ሳይማሩ አስተማሪዎች የሆኑት በልባቸው ድንዳኔ ነው። አንድ የማህበረ ቅዱሳን አመራርና መምህራቸው ያደረገውን ልንገራችሁ። መቼም ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው አይደል የሚባለው። ማን እንደሾመው በውል ባላውቅም ሲጠሩት መምህር ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ትሉታል። ታዲያ በአንድ ወቅት እንደ መምህራኖቹ ሊቅ መስሎ ለመታየት በጨርቅ መስሎት አለባበሱን አሳምሮ በአንድ ከባህር ማዶ ወደሚገኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቤተ መቅደስ ዘው ብሎ ጥልቅ ይላል። በዚያ የነበሩ አንድ አባት ስላላወቁት ማን ትባላለህ ብለው ይጠይቁታል እርሱም መምህር ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እባላለሁ ብሎ ይመልሳል። ታዲያ እኒህ አባት እንግዳ ዲያቆን መጣ ብለው እንኳን ደህና መጣህ፤ በል ከኛ ጋር ትቀድሳለህ እግዚአብሔርን አመስግን ቢሉት እርሱም አይ እኔ አልቀድስም አይሆንልኝም ብሎ እርፍ። እሳቸውም ምን ነው የኔ ልጅ ቢሉት፤ ቅዳሴ አልችልም ማስተማር ብቻ ነው የምችለው ብሎ እርፍ። እንደነገሩ ሁሉም አልፎ ስርዓተ ቅዳሴ ተጠናቅቆ ውጭ ከወጣ በኋላ እራሱን ሲያጋልጥ እኒህ አባት ተሐድሶ ናቸው፣ መናፍቅ ናቸው ብሎ ማስወራት ጀመረ። እንዲህ ነው እንግዲህ የተርታ ስም ሲያወጡ። ሲያጋልጧቸው ውጭ ወጥተው እያጋለጥን ነው ብለው ያወራሉ። ታዲያ ዳንኤል ክብረት ማን ነው? በእውነት ይንን ዲያቆን ትሉታላችሁ? መምህርነቱስ ከየት የመጣ ይሆን? ያላዋቂ ሳሚ ...

    እባካችሁ እናንተም ዲሊት እንዳታደርጉት ሌሎችም ይወቁት።

    ReplyDelete
  5. ጉድ ነው!!! ስምንተኛው ሺህ ገባ ብዙ ያሳየናል።

    ReplyDelete
  6. ere lebatekrestiyan kasebachu atsadebu enante man honachhehuna?

    ReplyDelete